ጥንታዊቷ የድቦ ኪዳነ ምህረት ገዳም ረጅም ዘመናት ያስቋጠረች ታሪካዊ ስፍራ በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ የምትገኝና ቀደም ሲል ጀምሮ የእግዚአብሔር ስም ሲጠራባት ስብሀተ እግዚአብሔር ሲደረስባትና ሰውና እግዚአብሀየር ሲነጋገሩባት የነበረች ቅድስት ቦታ ናት፡፡ ቀደም ሲል እግዚአብሔር ለህገ ኦሪት ሲያመልኩባት የኖረች ቦታ ስትሆን በአራተኛው ሽህ ክፍለ ዘመን በሰሎሞን ዘመነ መንግስት ካህናትና ሌዋውያን ኤፍሬምን ተከትለው አባይን ተሻግረው ጎጃም በገቡ ጊዜ መፅሀፍተ ኦሪትን ማስተማርና መስበክ የጀመረች በዛችው ቦታ ላይ እንደሆነ አባቶቻችን ታሪኩን አስቀምጠውልናል፡፡ በኋላም በዘመነ አዲስ አብርሃዎአጽብሃ የአባይን ወንዝ ተሻግረው ጎጃም በገቡ ጊዜ ያደሩባት ቦታ ድቦ ኪዳነ ምህረት ናት፡፡ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃንም ወንጌልን ካስተማሩና ከሰበኩ በኋላ ብዙ ህሙማን ቀርበው በጥምቀት ድህነት ባገኙ ጊዜ አብርሃዎአጽብሃ ከደወዌቸው ይፈውሱባታል በማለት ይህችን ቦታ በምህፃረ ቃል ድቦ ብለዋታል፡፡ ካህናት ግን ዲሂንቦ ይሏታል፡፡
አንድ ዮናክር የሚባል የትግራይ ተወላጅ ም/ደር እየሰበሰበ በዛችው ቦታ ላይ መፅሀፍት ኦሪትን ያስተምር ነበር፡፡ አብርሃዎአጽብሃና አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን በህዝቡ ፊት አስቀርበው የቅድስት ሩፋኤልን ዕለት ሰጥተው ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራ አዝዘዋል፡፡ መምህራንም ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተላዌ ክርስቶስ ይባል ብለው ከሰየሙና ለሶስት ቀናት ያህል ቃለ ወንጌልን ለምዕመናን ካስተማሩ በኋላ ሄደዋል፡፡ ከዚያም አባ ተላዌ ክርስቶስ የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን አሰርተው ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በ352 ዓ.ም አርፈዋል፡፡ እርሳቸውም ከአረፉ በኋላ በ525 ዓ.ም አፄ ካሌብ የመን ዘዋይ የሰማእታት ናግራንን ደም ተበቅሎ ሲመለስ አባ ፍሬ መስቀል የተባሉ ቅዱስ አባት አክሱም አግኝተውት በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጻለቸው ንጉስ ሆይ በጎጃም ክፍለ ሀገር ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራ ታቦት ሚካኤልን፣ ታቦተ ገብርኤልን፣ ታቦት ኪዳነ ምህረትን ይሰጠኝ ብለው አስፈቀዱት፡፡ ንጉሱም ይህንን በሰሙ ጊዜ በጣም ደስታ ተሰምቷቸው እነዚህን ታቦታት ከቤተ ርስቲያን አገልጋይ ካህናት ጋር የ5 ቀዳሲያን ልብስተ ተክህኖ በመጨመር ስምንት ወታደሮች አብረዋቸው እንዲሄዱ አዘዘ፡፡ ይህን የንጉሱን መልካም ፈቃድ በሰሙ ገዜ ታላቅ ደስታ ተሰማቸው፡፡ የተፈቀደላቸውን ታቦታት በመያዝና የታዘዙላቸውን ወታደሮች በማስከተል ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡
ጎጃም በደረሱ ጊዜ በእነብሴ ውስጥ በምትገኘው ድቦ በምትባለው አደሩ፡፡ አባ ፍሬ መስቀልም በዚያችው ቦታ 7 ቀን ከፀለዩ በኃላ መንፈስ ቅድሱ ስለተገለፀላቸው በእመቤታችን ቅድስት ድምንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን አሰርተው አገልግሎት ጀመሩ፡፡ በኋላም በ530 ዓ.ም ንጉሱ አፄ ገ/መስቀል በዘጠኙ ቅዱሳን አማካኝነት አድባራትና ገዳማት እንዲቋቋሙ አዋጅ አስተላለፉ፡፡ አባ ፍሬ መስቀል ይህንን በሰሙ ጊዜ በትግራይ ሀገረ ስብከት ወደምትገኘው ደብረ ዳሞ ሄደው አጼ ገ መስቀልን አግኝተው ገዳም እንዲያቋቁሙላቸው ጠየቁ፡፡ ንጉሱም ጥያቄቸውን ተቀብለው ልዩ ስሙን ደብረ መንኩራት ብለው ሰየሟት፡፡ በአሁኑ ጊዚ በድቦ ኪዳነ ምህረት ገዳም በቅዳሴና በዝማሬ እንዲሁም በሌሎች መንፈሳዊ ተግባራት ተሰማርተው የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ካህናት መነኮሳት የቅኔ መምህሮች እንዲሁም መርጌታዎች ይገኙባታል፡፡ በመሆኑም ይችን ጥንታዊትና ታሪካዊት ገዳም በየካቲት 16 ድቦ ኪዳነ ምህረት በዓሉ እንዲከበር ተደረገ፡፡
ይህ የተፈጥሮ መስህብ እንደ መጠሪያው እንዲህ ታላቅ መንፈሳዊ ሰው ጋር ግንኙነት አለው፡፡ ዋሻው አባ አርስኒዮስ ለአርባ አመታት ይፀልዩበት ነበር ቦታ ሲሆን በውስጡም እጅግ የሚያስገርሙና የሚስደምሙ የግድግዳ ላይ ቅርሳ ቅርስ አሉበት፡፡ እንደ አካባቢው ሰዎች ከላይ በዋሻው ውስጥ ታቦቶች ተደርድረውበት የነበሩ ወንበሮች እና የተሌዩ የተፈለፈሉ ስራዎች ይገኛሉ፡፡ በመግቢያው አካባቢ ባህር የመሰለ እጅግ የሚሥፈራራ ውሃ አለ፡፡ ውሃውም አባ አርስኒዮስ ለጸበል ይጠቀሙበት እንደነበር ይነገራል፡፡ ምንም እንኳ ውስጡን ሙሉ በሙሉ ሄዶ የጨረሰው ሰው ባይደግም በግምት እስከ የቀንዳች እንደሚደርስ ይነገራል፡፡ ይህም ከየቀንዳች ዋሻ ጋር ግንኙነት አላቸው፣ አንድ ዋሻ ናቸው ይባላል፡፡ ነግር ግን በውስጡ ዘንዶ እና የመሳሰሉ --------- አሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የተለያዩ ፅላቶች ተጠልለውበት ስለሚኖሩ እነደሆነ ይነገራል፡፡ የዋሻው አቀማመጥ እጅግ ዳገታማ ከመሆኑ አኳያ እጅግ አስፈሪ እና አስደንጋጭ መንገድ ነው፡፡
ይች ዛፍ ወይራ ስትሆን የምትገኘው ቁስቋማ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡ የዛች ዛፍ ታሪካዊና መንፈሳዊ አቋቋሟ እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ምክንቱም ቤተክርስቲያኗ በምትሰራበት ጊዜ ዛፏ የምትገኘው ከመሰረቷ ላይ ነበር፡፡ እናም በዚህም የተነሳ የአካባቢው ህዝብ ለመቁረጥ ተዘጋጅቶ ነበር ነገር ግን የመቁረጫ መሳሪዎች እንደ ምሳር /መጥረቢያ/ አይነት ስላልተዘጋጀ ለሚቀጥለው ቀን እንድትቆረጥ ተነገረ፡፡ በቀጠሮውም መሰረት ህዝቡ ለስራ በመጣበት ሰዓት ዛፏ ከቤተ ክርስቲኗ እጅግ እርቃ ተገኘች፡፡ ነግር ግን ስሯ እና መሰረቱ ከዚው ከነበረበት ቦታ ላይ ነው በዚህም የተነሳ ህዝቡ የቤተክርስቲኗን ኃይል እና ገድል ለመናገር ሲባል የግንድ አጥኒቱ ማርያም እየተባለች ዘፏም የግንድ አጥኒቱ ዛፍ ተብላ ትጠራለች፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ዘፏ ለቤተክርስቲኗ እድሳትና መስፋፋት እጅግ አስቸጋሪ ብትሆንም ካሏት ታሪካዊ ገድል ምክንያት ከዚያው ባለበት ቦታ ላይ ናት፡፡ ይህች ዛፍ የምትገኘው ከቁስቋም ቤተክርስቲየን ውስጥ ነው፡፡
ይህ ዋርካ የሚገኘው ከቁስቋም ቤተ ክርስቲያን ቁጥር ግቢ ውጭ ሲሆን እድሜውም 500 ዓመት እንደሆ ይነገራል፡፡ የተከለው ሰው ይሁን በተፈጥሮ የተገኘ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ እንደ መፅሀፍቶች ግን ዋርካ 750 ዓመት የመኖር አቅም ስላለው ይህም ዋርካ 500 ዓመት ሊሞላው /ሊሆነው/ ይችል ይሆናል፡፡
ከስሙ መረዳት እንደተቻለው ይህ ድንጋይ በሌላ ድንጋይ ላይ የተቀጠለ ሲሆን ርዝመቱም ወደ 3 ሜትር አካባባ ይሆናል፡፡ የሚገኝበት አካባቢ በጣም ገደላማ አካባቢ ስለሆነ እጅግ አስገራሚና ለአካባቢውም ግርማ ሞገስ ያላብሳል፡፡ የአካባቢው ወጣቶች በጣም ፀሀይ ባልሞቀችበት ሰዓት ድንጋይ ላይ በመውጣት ትርፍ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ፡፡ ከድንጋይ ላይ በመሆን የአካባቢውን መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ (በርቀትም እንዲሁም) መመልከትና ማድነቅ ይቻላል፡፡
ስለ ድንጋይ አፈጣጠር ሁለት የተለያዩ አስተያየቶችበአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ይንፀባረቃል፡፡ አንደኛው ወገን ድንጋዩ የተፈጠረው ከጊዜ ብዛት የተነሳ ጥቃቅንና ቀርጥራጭ ድንጋዮች በመጣመር ነው ይላሉ፡፡ ይህ ከሞላ ጎደል ከጆግራፊ ፅንሰ ሃሳብ ጋር ይዛመዳል፡፡ ሁለተኛው ወገን የድንጋዩን አፈጣጠር እጅግ ኃይማኖታዊ እና ከእግዚአብሔር ኃይል ጋር ያዛምዱታል፡፡ ይኸውም ይህ ቅጠል ድንጋይ የተፈጠረው ከላይ ወደ ታች በሚንከባለልበት ሰዓት እና ከዋናው /መሰረተ/ ድንጋይ ላይ ሲያርፍ በእግዚአብሔር ኃይል የረጋ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም በዚያ ሰዓት እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲያን እየሄዱ ስለነበር ነው፡፡ ክስተቱ የተፈጠረበት ዘመን በውል እንደማይታወቅ የአካባቢ ምንጮች ይገልፃሉ፡፡
ከዚህ ላይ ዋናው መግለፅ የምንፈልገው ነገር ቢኖር አካባቢው ለቱሪዝም እድገት የሚኖረው ጠቀሜታ እጅግ የጎላ ነው፡፡ ምክንያቱም በጣም የተለያዩ አይነት የእንስሳት እና የእፅዋት ዝርያዎች ከማራኪ መልዕካ ምድራዊ አቀማመጥ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡ አካባቢው ካለማጋነን ከሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርኮች ጋር እጅግ ተመሳሳይ ነው፡፡ ልዩነት የመታወቅ እና ያለመታወቅ ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡
ይህ ድንጋይ ከቅጥሉ ድንጋይ ባሻጋሪ የሚገኝ ሲሆን ሙዛሙዜው የሚባለው ስያሜ የሰሰጠው ከሙዝ ዛፍ ጋር ካለው ግንኙነት ነው፡፡ ማለትም ከድንጋይ ስር የሚፈልቅ ምንጭ ስላለ አካባቢው በሙዝ፣ በሸንኮራ አገዳ፣ ሸንበቆ የመሳሰሉ አታክልቶች የገለፅን አካባቢ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ ድንጋይ ከቅጠሉ ድንጋይ ጋር ሲነፃፀር ታሪካዊነቱና የተፈጥሮ መስህብነቱ በጣም ያነሰ ከመሆኑም በላይ አካባቢው እጅግ ገደላማ ከመሆኑ አኳያ ማንም የሚወጣበት ሰው የለም፡፡ ይህ ለአይን ብቻ ከሩቅ የሚፈቅድ ድንጋይ ነው፡፡ ከድንጋይ ስር ሲታይ ምንም ዓይነት መሰረት /አፈር ወይም ሌላ ድንጋይ/ በፍፁም የለም፡፡ ካለማጋነን የፊት ድንጋዮችን ያነሳ ----- ይመስላል፡፡
ይህ ዋሻ የሚገኘው ከላይ በተራ ቁጥር 5 ከገለፅነው ድንጋይ ስር ነው፡፡ ነፋሱ ዋሻ የሚለውን ስያሜ ያገኘው አካባቢው በተለይ ራሱ ዋሻው እጅግ ነፋስ የሚበዛበትና አንዳንድ ጊዜም ሰዎችን ያለፍላጎት ወደ ተሌየ ቦታ የሚንደረድር በጣም ነፈሳማ ቦታ ነው፡፡ የመግቢው ---- የተጌጠ ቤት መግቢያ የሚመስል ሲሆን የአካባቢውም ህብረተሰብ ብዙ አገልግሎት ይጠቀሙበታል፡፡ ይህንን ዋሻ ከአባ አርስንዮስ ዋሻ የሚያላያይ ዋና ነገርም ይህ ነው፡፡ ማለትም በዚህ ዋሻ ውስጥ የተለያየ ዓይነት ስራዎችን ማለትም ቡና ማፍላት፣ መተኛት፣ፍየልና ማሳደር ይቻላል፡፡
ምንጭ፡- የመርጡለ ማርያም ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት